አሜሪካ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች
የአሜሪካ ግምጃ ቤት፡ እርምጃው በዓለም አቀፍ ባንኮች ያለውን የተቋሙን ገንዘብ የሚያቀዘቅዝ ነው ብሏል

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፡ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በአገሩ ጥቅም ላይ እየተንቀሳቀሰ ነው በማለት አዲስ ማዕቀብ ጥሏል።
በተቋሙ አሠራር ላይ ቅሬታዋን ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ፡ ቀደም ሲል በሠራተኞቹ ላይ ማዕቀብ ማጽደቋን ዘገባዎች ያስረዳሉ።
እርምጃው በዓለም አቀፍ ባንኮች ያለውን የተቋሙን ገንዘብ የሚያቀዘቅዝ መሆኑን የአሜሪካ ግምጃ ቤት ገልጿል።
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በተወሰኑ መሪዎች ላይ ብቻ አተኩሮ ይሠራል በማለት የሚወቅሱ በርካታ አገራት አባልነታቸውን የማቋረጥ እርምጃ ሲወስዱ ቆይተዋል። በሐምሌ 2002 የተመሠረተው ፍርድ ቤቱ አሜሪካና ሩሲያን ጨምሮ በርካታ አገራትን አያካትትም።
