የኢትዮጵያ ኃይሎች ራማን ተቆጣጠሩ
ከአክሱም በኋላ ከኤርትራ ድንበር 7 ኪሎ ሜትር ብቻ የምትርቀው ራማ በቁጥጥር ስር መዋሏን ACLED ገለጸ።

የኢትዮጵያ ኃይሎች በትግራይ ያላቸውን ቁጥጥር እያስፋፉ መሆናቸውንና ታሪካዊቷን ከተማ አክሱምን ከያዙ በኋላ ራማንም መቆጣጠራቸውን ገለልተኛው የግጭት ክትትል ተቋም ACLED አስታወቀ።
ራማ የመረብ ለኸ ወረዳ መቀመጫ ስትሆን በመካከለኛው ትግራይ ዞን ትገኛለች፤ ከኤርትራ ድንበር 7 ኪሎ ሜትር ብቻ ትርቃለች። ከዓዲ ቋላ 25፣ ከዓድዋ 30፣ ከአክሱም ደግሞ 33 ኪሎ ሜትር ትርቃለች።
ACLED እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ ኃይሎችና አጋሮቻቸው ወደ በርካታ ስትራቴጂያዊ ከተሞች ከተስፋፉ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች በዛላምበሳ በኩል ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ውጊያው በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል አሁንም ቀጥሏል።
