ኤርትራ የተመድ የመከላከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀች
ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ፡ የኢትዮጵያ እርምጃ ለመላው ቀጣናው አለመረጋጋት የሚፈጥር ነው አሉ

ኤርትራ፡ ኢትዮጵያ የጦርነት አዋጅ ናት ያለችውን እርምጃ ተከትሎ፡ የተባበሩት መንግሥታት የመከላከያ እርምጃዎች እንዲወስድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ ጥሪ አቅርበዋል።
ዑስማን ሳልሕ ለጸጥታው ምክር ቤት በጻፉት ደብዳቤ፡ የኢትዮጵያ እርምጃ በሁለቱ አገራት ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ውድመት የሚያስከትልና ለመላው ቀጣናው አለመረጋጋት የሚፈጥር ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
ደብዳቤው የተጻፈው፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቅምት 9 ለጸጥታው ምክር ቤት ባስተላለፈው መልእክት፡ ለሦስት ዓመታት በኤርትራ ላይ ያወጀውን ጦርነት ለመተግበር እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ካስታወቀ በኋላ ነው።
ኤርትራ በራስ መከላከል በሚል የሚቀርበው ማብራሪያ ባዶና አሳሳች መሆኑን በመግለጽ፡ ጸጥታው ምክር ቤት በተመድ ቻርተር ምዕራፍ 7 መሠረት አግዳቢ እርምጃዎች እንዲወስድ ጠይቃለች።
