ግብጽ በሪያድ አውሮፕላን ማረፊያ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘች
ሦስት ሰዎች ተገድለዋል፤ ግብጽ ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር ሙሉ ትብብር እንደምታደርግ አስታወቀች

Saudi Arabia's General Authority of Civil Aviation says 12 people were killed and 309 wounded in the missile attack on King Khalid International Airport. The Saudi-led coalition blamed Yemen's Houthis and called it a war crime, Saudi Arabia said it would retaliate firmly, and flights at the airport remain suspended, Al Jazeera reported.
ግብጽ የንጉሥ ካልድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ዒላማ አድርጎ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ ጠንካራ ውግዘት ማሰማቷን ኢጂፕት ቱዴይ ገልጿል።
በሪያድ የንጉሥ ካልድ አውሮፕላን ማረፊያንና የሳዑዲ ዓረቢያ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን ዒላማ አድርጎ በተፈጸመው ጥቃት፡ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መጎዳታቸውን ድረ ገጹ አስታውቋል።
ግብጽ በሰጠችው መግለጫ፡ ዓለም አቀፍ ሕግን በመጣስ የተፈጸመውን ይህን ጥቃት አጥብቃ በማውገዝ፡ ጸጥታንና ሉዓላዊነትን እንዲሁም የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ከመንግሥቱ ጋር ሙሉ በሙሉ እንደምትተባበር አስታውቃለች።
ጥቃቱ አውሮፕላኖችን ዒላማ ያደረገና ዓለም አቀፍና አካባቢያዊ ጸጥታንና መረጋጋትን የሚያሳንስ መሆኑን የገለጸችው ግብጽ፡ ለሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥትና ሕዝብ መጽናናትን፡ ለተጎዱትም ፈጣን ማገገምን ተመኝታለች።
