ሳዑዲ ዓረቢያ በሰንዓና በሦስት የየመን ክፍለ ሀገራት የአየር ጥቃት አደረሰች ሲሉ ሑቲዎች ገለጹ
ጥቃቱ ሑቲዎች በመዲና ላይ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ላይ ለፈጸሙት ጥቃት የተወሰደ አፀፋ ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቶች ያመለክታሉ

An AFP journalist reported seeing flames and smoke near an Aramco refinery south of Riyadh at about 20:07 local time on Saturday. Saudi authorities and Aramco have not confirmed the cause, and no group has claimed responsibility. The Houthi-affiliated outlet Almasirah said Saudi Arabia carried out 26 military operations against Sanaa on Saturday, with explosions heard through the day. Reuters reported on Friday that Riyadh may be preparing a wider offensive, partly to regain control of the Bab al-Mandab Strait.
የየመን ሑቲ ቡድን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ በመዲናዋ ሰንዓ እና በሳዓዳ፣ በታይዝና በዓምራን ክፍለ ሀገራት ላይ የአየር ጥቃት ማድረሷን ገለጸ።
በሑቲ የሚመራው የሳባ የዜና ወኪል፣ አውሮፕላኖቹ በሦስቱ ክፍለ ሀገራትና በመዲናዋ ሰንዓ በርካታ ቦታዎችን ዒላማ ማድረጋቸውን አስታውቋል። የቡድኑ ወታደራዊ ተናጋሪ በበኩሉ፣ በ24 ሰዓታት ውስጥ 47 ጥቃቶች መፈጸማቸውን ገልጿል። የደረሰውን ጉዳት የሚመለከት ዝርዝር አልተሰጠም።
በሳዑዲ ዓረቢያ የሚመራው ጥምረት ተናጋሪ ብርጋዴር ጄነራል ቱርኪ አል-ማሊኪ፣ ወደ ሳዑዲ ከተሞች ካሚስ ሙሻይትና ጃዛን የተተኮሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችና ባሊስቲክ ሚሳይሎች በአየር መከላከያ መመከታቸውን አስታውቀዋል። ሑቲዎች ከሁለት ቀናት በፊት በመዲና የሚገኘውን የታይባ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ዒላማ ማድረጋቸውንም ጠቅሰዋል።
የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኃይል ማመንጫው ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ ማውገዙንና ሳዑዲ ዓረቢያ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ የምትወስዳቸውን እርምጃዎች እንደሚደግፍ አስታውቋል።
የተጠቀሱት ቁጥሮችና ዒላማዎች ከሑቲ ወገን የወጡ ናቸው፤ ናትና ቲቪ በራሱ ሊያረጋግጣቸው አልቻለም።
