ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ በተባበሩት መንግሥታት፡ የአፍሪካን ቀንድ ያናወጠው ጦርነትና በሰብአዊ ድጋፍ ስም የሚደረግ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም ጠየቁ
በኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የተሰራጨው መግለጫ በአፍሪካ ቀንድ ያለችን አንዳችም ሀገር በስም አልጠቀሰም።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልሕ መሐመድ በኒው ዮርክ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ 81ኛ ስብሰባ ያደረጉትን መግለጫ ሙሉ ጽሑፍ አውጥቷል።
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ መሐመድ፡ መስከረም 28 በኒው ዮርክ በተካሄደው 81ኛው መደበኛ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መግለጫ አቀረቡ። የአፍሪካ ሕዝቦች፡ "ዝርፊያ፡ ጭቆናና ማታለል መለያው የሆነው የዜሮ-ሳም ዓለማዊ ሥርዓት ዋነኛ ተጠቂዎች" መሆናቸውን ገልጸው፤ "በሰብአዊ ድጋፍ ስም የሚደረግ አድካሚ ጣልቃ ገብነት" እንዲቆም ጠይቀዋል። በተጨማሪም፡ "በሰፊው ጎረቤታችን፡ ይኸውም በናይል ተፋሰስ፡ በአፍሪካ ቀንድ፡ በቀይ ባሕር፡ በአደን ባሕረ ሰላጤና በባሕረ ሰላጤው ሀገራት ሁከት ለመፍጠር የተቀሰቀሰው ጦርነትና ተያያዥ የማፍረስ ተግባራት" እንዲቆሙ ጠይቀዋል። በማስታወቂያ ሚኒስቴር የተሰራጨው መግለጫ፡ በአፍሪካ ቀንድ ያለችን አንዳችም ሀገር በስም አልጠቀሰም። እንዲሁም ስለ "የፕሬዝዳንት ትራምፕ ግልጽ የሆነው የMAGA ዶክትሪን"፡ የኢራን ግጭትና የዩክሬን ጦርነት በመጥቀስ፡ አፍሪካውያን "ተገቢ ስትራቴጂዎችን እንዲቀይሱ" እና "ያለፉና እንቅፋት የሆኑ መዋቅሮችን እንዲያስወግዱ" አበረታተዋል።
