ብሉምበርግ፦ ኢትዮጵያ ከ3,000 በላይ ወታደሮችን ከሶማሊያ ለማስወጣት አቅዳለች፤ ሶማሊያ ምንም መረጃ አልተሰጠኝም ብላለች
ብሉምበርግ ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮችን ጠቅሶ፣ ማስወጣቱ በቀናት ወይም በሳምንታት ውስጥ ሊጀመር ይችላል ብሏል። የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣን በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ስለማንኛውም የወታደር ማስወጣት ዕቅድ አላሳወቀችንም ብለዋል።

Bloomberg reported on 30 September that Ethiopia plans to pull more than 3,000 troops out of Somalia and redeploy them to the war in the north. A Somali defence ministry official said Ethiopia had not informed Mogadishu of any withdrawal plan.
ብሉምበርግ መስከረም 30 እንደዘገበው፣ ኢትዮጵያ ከ3,000 በላይ ወታደሮችን ከሶማሊያ ለማስወጣትና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከፌደራል ሠራዊቱ ጋር እየተዋጉ ባሉ የታጠቁ ቡድኖች ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ አቅዳለች። ተቋሙ፣ በይፋ ለመናገር ያልተፈቀደላቸውንና ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮችን ጠቅሶ፣ ወታደሮቹ በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት መውጣት ሊጀምሩ ይችላሉ ብሏል።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣን በበኩላቸው፣ “ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ ለማስወጣት ያላትን ማንኛውንም ዕቅድ አላሳወቀችንም” ብለዋል።
ዕቅዱ በአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልእኮ በሶማሊያ (AUSSOM) ውስጥ የሚያገለግሉትን የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ ወይም በሁለትዮሽ ስምምነት የተሰማሩትን፣ አሊያም ሁለቱንም የሚመለከት መሆኑ አልተገለጸም። ከሁለቱ መንግሥታት አንዳቸውም የወታደር ማስወጣት በይፋ አላስታወቁም።
ዘገባው የወጣው የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ አዲስ አበባን ከጎበኙ በኋላ ነው። ዘገባው በገለልተኛ አካል ሊረጋገጥ አልቻለም።
