ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ጦርነቱ ወደ አዲስና ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገለጹ
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት፣ ወደ ትግራይ የገቡት ኃይሎች የመግቢያ መንገዳቸውን እንጂ የመውጫቸውን አያውቁም ሲሉ ተናግረዋል

In a video message reported by AFP on Friday, TPLF chairman Debretsion Gebremichael said "the war is regional and it is a war to control the Red Sea". Al Jazeera reported that he acknowledged federal forces had occupied parts of the region but said his forces would counter-attack "in due course".
የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ወደ አዲስና ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን ሐሙስ ምሽት ገለጹ።
ወደ ትግራይ የገቡት የፌደራል ጦርና አጋር ኃይሎች የመግቢያ መንገዳቸውን እንጂ የመውጫቸውን አያውቁም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ክልሉ ወራሪ ኃይል ብለው የጠሩት ኃይል መቃብር እንደሚሆን አክለዋል።
እየተካሄደ ያለው ጦርነት በትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከአጋር ኃይሎች ጋር በመቀናጀት እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል። የትግራይ ኃይሎች በራያ፣ በአላማጣ፣ በጨርጨር፣ በወጀራትና በአበርገለ ግንባሮች ቦታዎችን ይዘው እየተከላከሉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው፣ የፌደራል ኃይሎች ወደ መቀለ መቃረባቸውንና በዓፋር አቅጣጫ የሚገኙ ክፍሎቹ ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ያህል መቅረባቸውን እየዘገቡ ነው። ናትና ቲቪ እነዚህን ዘገባዎች በራሱ ሊያረጋግጥ አልቻለም።
ዶ/ር ደብረጽዮን በመጨረሻም ሕዝቡ ከወታደራዊ ተቋማትና መሠረተ ልማቶች እንዲርቅና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
