ቻይናና ጅቡቲ ስለ ቀይ ባሕር የጋራ መግለጫ አወጡ
የቀይ ባሕር አስተዳደርና ደህንነት አዋሳኝ አገራትን ብቻ እንደሚመለከት አረጋግጠዋል።

ቻይናና ጅቡቲ ሁሉም አገራት በባብ ኤል መንደብ መሽጎጥ የባሕር ጉዞ ነፃነት እንዲጠቀሙና፣ የቀይ ባሕር አስተዳደርና ደህንነት ደግሞ አዋሳኝ አገራትን ብቻ እንደሚመለከት በጋራ አረጋግጠዋል።
መግለጫው የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቤጂንግ ካደረጉት ስብሰባ በኋላ የወጣ ነው። ሁለቱም ወገኖች ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የጋራ እምነታቸው መሆኑን አስምረዋል።
በቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኙ አገራት ፍላጎት ሊከበርና በቀጠናው የደህንነት ስጋቶች ላይ ማንኛውም ውጥረት ሊወገድ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ይህ አቋም ከኤርትራ፣ ከግብፅ፣ ከሱዳንና ከሶማሊያ አቋም ጋር የሚስማማ መሆኑ ተገልጿል። ቻይና በ2017 በጅቡቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአገሯ ውጭ ወታደራዊ ሰፈር መክፈቷ ይታወሳል።
