ጋና ያልተቀነባበረ ማዕድን ወጪ ንግድን ልትገድብ ነው
ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ዕቅዱ እስከ 2030 እንደሚተገበርና የኢንዱስትሪ ምርትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ገለጹ።

ጋና የሀገር ውስጥ ምርትን ለማሳደግ ያልተቀነባበረ ማዕድን ወደ ውጭ መላክን ልትገድብ መሆኑን አስታውቃለች።
እስከ 2030 የሚተገበረው ዕቅድ የኢንዱስትሪ ምርትን ለማሳደግ አጋዥ እንደሚሆን የጋና ፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ጠቁመዋል።
ያልተቀነባበረ ብረት፣ ሊቲየም፣ ቦክሳይትና ማንጋኒዝ በቅድሚያ ከሚከለከሉ ማዕድናት መካከል መሆናቸውን አስረድተዋል።
የዕቅዱ አካል ሆኖ አገራቸው ማዕድን ለማቀነባበር የሚያስችል መሠረተ ልማትና ቴክኖሎጂ እንደምታስፋፋ አስታውቀዋል። ጋና በወርቅ ምርት በአፍሪካ አንደኛ፣ በዓለም ደግሞ ስድስተኛ ደረጃ ትይዛለች።
