ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ለውይይት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
ኢትዮጵያ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የምትሰጠውን ድጋፍ ካቆመች ብቻ ነው ሲሉ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የሚሰጠውን ድጋፍ የሚያቆም ከሆነ ከአዲስ አበባ ጋር ወደ ውይይት ለመግባት ዝግጁ መሆኗን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሕየዲን ሳልም መግለጻቸውን የሱዳን ዜና ወኪል (ሱና) አስታወቀ።
ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት በሱዳንና በአፍሪካ ቀንድ የፈረንሳይ ልዩ መልዕክተኛ ዣን-ማሪ ሳፋ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በሱዳን ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባና ለማንኛውም ወገን ወታደራዊ ድጋፍ እንደማይሰጥ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።
በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ውጥረት ከዚህ ቀደምም በከባድ ክሶች ታጅቦ ቆይቷል።
