ሶማሊያ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ባለው ውጥረት ገለልተኝነቷን አወጀች
የሞቃዲሾ አቋም ሰላምን በመጠበቅና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ላይ የተመሠረተ ነው ተብሏል።

ሶማሊያ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ በመጣው ወታደራዊ ውጥረትና አለመግባባት ገለልተኝነቷን እንደምትጠብቅ በይፋ አስታወቀች።
ውሳኔው የመጣው በሰሜን ኢትዮጵያ እንደገና የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ ሰፊ ቀጣናዊ ግጭት እንዳያድግ ሥጋቶች በበረቱበት ወቅት ነው።
የሶማሊያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐሰን መሐመድ ዓሊ ናዳራ ለቢቢሲ ሶማሊ እንደገለጹት፡ የሞቃዲሾ አቋም ሰላምን በመጠበቅ፡ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበርና ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለውን ትብብር በመቀጠል ላይ የተመሠረተ ነው።
