የሩስያ ነዳጅ ወደ ዓለም ገበያ ተመለሰ
በፑቲንና ትራምፕ መካከል ከተደረሰው ስምምነት በኋላ አሜሪካ ማዕቀቡን እስከ ሚያዝያ 2027 አራዘመች።

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደረሱበት ስምምነት በኋላ የሩስያ ነዳጅ ምርቶች ወደ ዓለም ገበያ መሸጥ መጀመራቸው ተገለጸ።
ሁለቱ መሪዎች ጥቅምት 9 ባደረጉት የስልክ ውይይት ሩስያ ለዓለምና ለአሜሪካ ገበያ ነዳጅ እንድታቀርብ መስማማታቸው ይታወሳል።
በስምምነቱ መሠረት ሩስያ በዚህ ወር 300 ሺህ፣ በሚቀጥለው ወር 500 ሺህ፣ በታኅሣሥ ደግሞ አንድ ሚሊዮን ቶን ናፍጣ ወደ ዓለም ገበያ ታቀርባለች።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት በሩስያ ነዳጅ ላይ የነበረውን ማዕቀብ እስከ ሚያዝያ 2027 በማራዘም ጊዜያዊ ፈቃድ ሰጥቷል።
