ሩሲያና ኢራን ስትራቴጂያዊ ስምምነታቸው አዎንታዊ ውጤት እያስገኘ ነው አሉ
የንግድ ልውውጣቸው ከ20 በመቶ በላይ አድጓል፤ ፑቲን ስለ ኢራን ጦርነት ተናግረዋል

ሩሲያና ኢራን ባለፈው ዓመት መጀመሪያ የተፈራረሙት አጠቃላይ ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት አዎንታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሁለቱ አገራት መሪዎች ጥቅምት 8 በቱርክሜኒስታን ባደረጉት ውይይት፡ የአገራቸው የንግድ ልውውጥ ባለፈው ዓመት ከ20 በመቶ በላይ ማደጉን ገልጸዋል። የንግድ እንቅስቃሴው ባለፉት ስምንት ወራት አዎንታዊ ግስጋሴ ማሳየቱንም አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና ፕሬዝዳንት መስዑድ ፐዘሽክያን በውይይታቸው፡ በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን በጸጥታና በሌሎች ዘርፎች የተደረሱ ስምምነቶችም በቅደም ተከተል እየተተገበሩ መሆኑን አስረድተዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በተጨማሪ፡ ሩሲያ የኢራንን ጦርነት በሰላም ለማስቆም ሚናዋን እንደምትወጣ ገልጸዋል። ጦርነቱ ለመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃም ችግር መፍጠሩን በመጥቀስ፡ አሜሪካና ኢራን በውይይት እንዲያቆሙት አሳስበዋል።
