ኦፔክ፡ የነዳጅ ፍላጎት ዕድገት በ71 በመቶ መቀነሱን ገለጸ
ከ1.4 ሚሊዮን በርሜል ወደ 400 ሺህ በርሜል በቀን ወርዷል።

በ2026 በቀን 1.4 ሚሊዮን በርሜል ገደማ ይደርሳል ተብሎ የተገመተው የነዳጅ ፍላጎት ዕድገት ወደ 400 ሺህ በርሜል መውረዱን የነዳጅ አምራችና ላኪ አገሮች ድርጅት (ኦፔክ) አስታወቀ።
አኃዙ ቀደም ሲል ከተገመተው በ71 በመቶ መቀነሱን ድርጅቱ ገልጿል።
በኢነርጂ ዘርፍ የተደረገው ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት፡ እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅና በአውሮፓ የተከሰተው የጸጥታና ወታደራዊ ቀውስ ከምክንያቶቹ መካከል መሆናቸው ተነግሯል።
በ2027 የነዳጅ ፍላጎት ዕድገት በቀን ወደ 1.7 ሚሊዮን በርሜል ከፍ ሊል እንደሚችል የባለሙያዎች ግምት አለ።
የነዳጅ ዋጋ በዓለም ገበያ 100 ዶላር በበርሜል መድረሱን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
