በለንደን ወደ እስራኤል የሚደረግ የጦር መሣሪያ ሽያጭ እንዲቆም ሰልፍ ተካሄደ
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የንግድ ማዕቀብም እንዲጣል ጠይቀዋል

ብሪታንያ ለእስራኤል የምታደርገውን የጦር መሣሪያ ሽያጭ እንድታቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥቅምት 11 በለንደን ከተማ ተካሂዷል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች፡ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ብቻ ሳይሆን አገራቸው በእስራኤል ላይ የንግድ ማዕቀብ እንድትጥል ጠይቀዋል።
ብሪታንያ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የጀመረችውን ወታደራዊ ዘመቻ ተከትሎ የምትልከውን የጦር መሣሪያ መጠን መቀነሷ የሚታወቅ ሲሆን፡ ሙሉ በሙሉ እንድታቆም ሰልፈኞቹ ተማጽነዋል።
ብሪታንያ በጋዛ የሚካሄደውን ወታደራዊ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን፡ በምዕራብ ዳርቻ የሚደረገውን ሕገወጥ የሰፈራ መስፋፋትም እንደምትቃወም ይታወቃል።
