አሜሪካ ከኢራን ጥያቄዎች በከፊል መቀበሏ ተገለጸ
እርምጃው ግን የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤን ለመክፈት በቂ አይደለም ብለዋል የኢራን የጸጥታ ባለሥልጣናት።

አሜሪካ የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤን ለመክፈት ከቀረቡት ጥያቄዎች በከፊል መቀበሏን ኢራን አስታወቀች።
ሆኖም እርምጃው ዲፕሎማሲያዊ ምኅዳር ከመክፈት ባለፈ የውሃ መስመሩን ለመክፈት በቂ አለመሆኑን የኢራን የጸጥታ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
ኢራን መስመሩን የምትከፍት ከሆነ፡ በእሷ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ፡ አሜሪካና እስራኤል በመካከለኛው ምሥራቅ የሚያካሂዱት ወታደራዊ ዘመቻ እንዲቆም፡ ከወደቦቿ የመርከብ እንቅስቃሴን ለማገድ የተወሰደው እርምጃ እንዲነሳና የታገደው ገንዘቧ እንዲለቀቅ የሚያካትቱ 7 ጥያቄዎችን አቅርባለች።
አሜሪካ የትኞቹን ጥያቄዎች እንደተቀበለች የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ እስካሁን የለም። በኢራንና በአሜሪካ መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት የሰላም ንግግሩን እንዳደናቀፈው ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
