ኢራን በሳዑዲ ዓረቢያና በሁቲ መካከል ንግግር እንዲደረግ ጠየቀች
ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋኢ፡ በሁለቱ መካከል ለውይይት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጁ ነን ብለዋል።

ሳዑዲ ዓረቢያና የየመኑ ታጣቂ ቡድን ሁቲ ወደ ጠረጴዛ ቀርበው ንግግር እንዲያደርጉ ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋኢ በድጋሚ ገለጹ።
ባጋኢ በሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው፡ በአረቢያ ባሕረ ሰላጤ እየተካሄደ ባለው ግጭት ያላቸውን ከፍተኛ ሥጋት ከገለጹ በኋላ፡ ኢራን በሳዑዲና በሁቲ መካከል ደም አፋሳሽ ግጭት እንዲቀጥል እንደማትቀበል አስረድተዋል።
ይህ የተገለጸው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዓባስ አራግቺ ከሳዑዲ አቻቸው ጋር ባደረጉት የስልክ ንግግር አገራቸው ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጁ መሆኗን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
