የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንቨስትመንት የዓለምን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ብሏል IMF
በ2027 የዓለም ኢኮኖሚ በሦስት በመቶ ገደማ ሊያድግ እንደሚችል ተገምቷል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ እየተደረገ ያለው ግዙፍ ኢንቨስትመንት በዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጠቁሟል።
በ2027 የዓለም ኢኮኖሚ በሦስት በመቶ ገደማ ሊያድግ እንደሚችል የገመተው ድርጅቱ፡ ትልቁ ድርሻ በቴክኖሎጂ እየተደረገ ባለው ኢንቨስትመንት እንደሚወሰን አስረድቷል።
በዚህ ኢንቨስትመንት ምክንያት የእስያ ኢኮኖሚ ቀደም ሲል ከተገመተው በአንድ በመቶ ገደማ ሊያድግ እንደሚችልም ገልጿል።
ቻይና፡ ደቡብ ኮሪያ፡ ጃፓንና ታይላንድ የሚገኙባቸው የእስያ አገሮች በዘርፉ ግዙፍ ኢንቨስትመንት እያካሄዱ መሆኑ ተጠቅሷል።
በዓለም ደረጃ በ2026 በዚህ ዘርፍ 2.7 ትሪሊዮን ዶላር ገደማ መፍሰሱን የሚጠቅሱ ሪፖርቶች፡ አኃዙ በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3.5 ትሪሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ያመለክታሉ።
