የአውሮፓ ኅብረት በሩስያ ላይ ትልቁን ማዕቀብ ሊወስን ነው
አዲሱ እርምጃ ወታደራዊ ኢንዱስትሪን በተለይም የጦር መሣሪያ ምርትን ዒላማ ያደረገ ነው።

የአውሮፓ ኅብረት ከዚህ ቀደም ካጸደቀው ሁሉ ትልቁ ነው ያለውን ማዕቀብ በሩስያ ላይ እንደሚወስን አስታወቀ።
አዲሱ እርምጃ ወታደራዊ ኢንዱስትሪን በተለይም የጦር መሣሪያ ምርትን ዒላማ ያደረገ መሆኑን የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ገልጸዋል።
ማዕቀቡ ተግባራዊ ሲሆን የሩስያ የሚሳይል ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጎዳ ሚኒስትሮቹ ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ ዕቅዱ ለዩክሬን ጦርነት መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል የገለጸው የሩስያ መንግሥት፡ ኅብረቱ ጠበኛ እርምጃዎችን ከመውሰድ እንዲቆጠብ ጠይቋል። ማዕቀቡ ከተተገበረ በአውሮፓ ኅብረት ላይ ከባድ ኢኮኖሚያዊ ጠባሳ የሚያስከትል የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።
የአውሮፓ ኅብረት የዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በሩስያ ላይ 21 ዙር ማዕቀብ ማጽደቁንና ሩስያም ተመጣጣኝ ምላሽ መስጠቷን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
