ግብጽ፡ ኢትዮጵያ ኤርትራን እየወረረች ዝም ብዬ አላይም አለች
ጋዜጠኛ ካልድ መሐመድ፡ በቀይ ባሕር የሚወሰድ ማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ የአካባቢውን ሚዛን ያናጋል አለ

የግብጽ ጸሐፊና ጋዜጠኛ ካልድ መሐመድ፡ ኢትዮጵያ ለቀይ ባሕርና ለቀንደ አፍሪካ ቀጥተኛ ስጋት እየሆነች ግብጽ ዝም ብላ እንደማትመለከት ጽፏል።
ጸሐፊው፡ ግብጽ ኢትዮጵያ የትግራይን ጦርነት ለማስፋት ወይም ከኤርትራ ጋር ለመጋጨት የምታደርጋቸውን ሙከራዎች በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን አብራርቷል።
በቀይ ባሕር የሚወሰድ ማንኛውም አዲስ ወታደራዊ እርምጃ ወይም በኤርትራ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ላይ የሚደርስ ስጋት፡ የአካባቢውን የኃይል ሚዛንና የባሕር መስመር ጸጥታ እንዲሁም የግብጽን ከኤርትራ፡ ሱዳንና ሶማሊያ ጋር ያላትን ግንኙነት በቀጥታ የሚነካ መሆኑን ገልጿል።
በመጨረሻም፡ በኢትዮጵያ ሥርዓት የሚመታው የጦርነት ከበሮ መቀጠሉን ከተናገረ በኋላ፡ እንዲህ ዓይነቱ ጦርነት ለሥርዓቱና ለኢትዮጵያ ሕዝብ አውዳሚ መዘዝ እንዳለው አስጠንቅቋል።
