ቻይናና የአውሮፓ ኅብረት የንግድ ልዩነታቸውን ለማጥበብ ተወያዩ
በ2025 ከ860 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተለዋውጠዋል፤ ወደ አንድ ትሪሊዮን ለማድረስ አቅደዋል

የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክና የአውሮፓ ኅብረት የንግድ ልዩነታቸውን ለማጥበብ የሚረዳ ተጨማሪ የምክክር ውይይት ትናንት ጥቅምት 9 አካሂደዋል።
በቻይና የተካሄደው ውይይት የንግድ ግንኙነትን በማሻሻል፡ እንዲሁም የቀረጥና የኢንቨስትመንት መጠንን በመቆጣጠር ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።
ሁለቱም ወገኖች በቀረጥ ጉዳይ በመካከላቸው የተፈጠረውን የንግድ አለመግባባት ለማርገብ ተደጋጋሚ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል፤ ባለፈው ሰኔ ወር መጨረሻም ተወያይተው ነበር።
በ2025 ከ860 ቢሊዮን ዶላር በላይ የንግድ ልውውጥ ማካሄዳቸውን በመግለጽ፡ ቁጥሩን በዚህ ዓመት ወደ አንድ ትሪሊዮን ዶላር ለማድረስ ማቀዳቸውን ይጠቅሳሉ። የአውሮፓ ኅብረት ከቻይና ትልልቅ የንግድ አጋሮች አንዱ ነው።
