ቻናል 4 ስለ ኤርትራ ሠራዊት ባሰራጨው ዘገባ ይቅርታ ጠየቀ
ዋና አዘጋጅ ሊንድሲ ሂልሰም፡ የተጠቀምንበት ቪዲዮ የአሁኑ አልነበረም አለች

የቻናል 4 ዋና አዘጋጅ ሊንድሲ ሂልሰም፡ የምትመራው የዜና ማዕከል ያቀረበው የኤርትራ ሠራዊት ኢትዮጵያን ወረረ የሚለው ዘገባ የተጠቀመበት ምስልና ቪዲዮ ሐሰት መሆኑን በመግለጽ ይቅርታ ጠይቃለች።
ቻናል 4 የኤርትራ ሠራዊት ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል በማለት ምስልና ቪዲዮ አያይዞ ማሰራጨቱ የሚታወቅ ሲሆን፡ ከተለያዩ ወገኖች ማስረጃ ተብሎ የቀረበው ምስልና ቪዲዮ ሐሰት መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።
ከዚያ በኋላ ዋና አዘጋጇ በኤክስ ገጿ ባሰፈረችው ጽሑፍ፡ የተጠቀምንበት ምስል የአሁኑ መሆኑን ሳናረጋግጥ መረጃ አሰራጭተናል፤ በፈጸምነው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን ብላለች። ይዘቱ ከገጻቸው እንደሚነሳም ገልጻለች።
ቻናሉ በጥር 2023 የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ሲወጣ የሚያሳይ ምስል ከማኅደሩ አውጥቶ፡ ባለፉት ቀናት የኤርትራ ሠራዊት ኢትዮጵያን እየወረረ ነው በማለት እንዳሰራጨው ለማወቅ ተችሏል።
