ከባድ የጭነት በረራዎች ወደ ኤርትራ፡ ሱዳንና ኢትዮጵያ
ጥቅምት 4 የቤላሩስ IL-76 በምጽዋ አውሮፕላን ማረፊያ ታይታለች፤ ኤምሬትስ ወደ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ በረራ እያደረገች ነው

ኤርትራ፡ ሱዳንና ኢትዮጵያ በርካታ ከባድ የጭነት በረራዎችን እየተቀበሉ መሆኑ ተገልጿል።
ጥቅምት 4፡ የቤላሩስ ሩቢስታር አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በምጽዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መታየቷን፡ በምሥራቅ አፍሪካ የሚደረጉ በረራዎችን የሚከታተለው ጸሐፊ ሪች ቴድ በኤክስ ገጹ ገልጿል።
በተመሳሳይ፡ የሱዳን ሠራዊት ከጥቅምት 8 ጀምሮ ሰባት የጭነት አውሮፕላኖችን ከቱርክ መቀበሉን፡ የግብጽና የሩሲያ አውሮፕላኖችም ወደ ፖርት ሱዳን ተመላልሰው መግባታቸውን አስታውቋል።
ወደ ኢትዮጵያም፡ ከኤምሬትስ አል ዐይን አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ቦሌ በጥቅምት 8 እና 9 ተደጋጋሚ በረራዎች መደረጋቸውን አረጋግጧል። በብሪታንያ የኤርትራ ኤምባሲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ያሬድ ተስፋይ በበኩሉ፡ ኤምሬትስ በመላው ቀንደ አፍሪካ ጎጂ ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገልጿል።
