የአሜሪካ የዋጋ ግሽበት 3.7 በመቶ መድረሱ ተገለጸ
ካለፈው ዓመት በ1 በመቶ በላይ ጨምሯል፤ ምክንያቱ የነዳጅ ዋጋ ንረት ነው ተብሏል።

በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት የኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበት መጠን 3.7 በመቶ መድረሱን ሪፖርቶች ገለጹ።
አኃዙ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ1 በመቶ በላይ መጨመሩን የገለጹት ሪፖርቶቹ፡ ምክንያቱ የመሠረታዊ ፍላጎቶች ዋጋ ንረት በአጠቃላይ፡ የነዳጅ ዋጋ ንረት ደግሞ በተለይ መሆኑን አስረድተዋል።
ክስተቱ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል የገለጸው የአሜሪካ መንግሥት፡ ለማቃለል እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
