ትራምፕ፡ በቀጠር በኩል ከኢራን ጋር የሚደረግ ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት በዚህ ሳምንት ሊጀመር ይችላል አሉ
የኢራንን ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ የመጣ ንግግር።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በቀጠር አደራዳሪነት ከኢራን ጋር የሚደረግ ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት በዚህ ሳምንት ሊጀመር እንደሚችል ለአሜሪካዊው የዜና ድረ ገጽ አክሲዮስ ጠቁመዋል።
ይህን ያሉት፣ የኢራንን የሰባት ቀን የሰላም ሃሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ኢራናውያን ስምምነት ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን እኔ የምፈልገው ዓይነት አይደለም በማለት፣ ያላቸውን እድል በአግባቡ አልተጠቀሙበትም ሲሉ ገልጸዋል።
ትራምፕ በተጨማሪም፣ አሁንም ወታደራዊ እርምጃ የመውሰድ አማራጭን እያሰቡ መሆኑን አስጠንቅቀዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው፣ አገራቸው አሁንም ለውይይት ዝግጁ መሆኗንና በቀጠር አደራዳሪዎች በኩል የአሜሪካን ይፋዊ መልስ እየጠበቀች መሆኗን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
