ሱዳን የወርቅ ቆፋሪዎችን ግድያ ልታጣራ ነው
አል-ቡርሃን ከግብፅ ድንበር አቅራቢያ ለተፈጸመው ‘አሳዛኝ ክስተት’ ከፍተኛ ኮሚቴ አቋቋሙ።

የሱዳን መሪ አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን ከግብፅ ድንበር አቅራቢያ የተፈጸመውንና ‘አሳዛኝ ክስተት’ ሲሉ የገለጹትን የሱዳናውያን የወርቅ ቆፋሪዎች ግድያ እንዲጣራ ጥሪ አቀረቡ። ይህን የሚያከናውን ከፍተኛ ኮሚቴ ማቋቋማቸውንም አስታውቀዋል።
ከማዕድን ቦታው ሪፖርት ያቀረቡ የዜና ተቋማት እንደገለጹት ጥቅምት 10 ቅዳሜ ጠዋት የግብፅ ተዋጊ አውሮፕላኖች ወደ ማዕድን ቦታው በመምጣት በባህላዊ ቆፋሪዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፤ በዚህም ከ72 በላይ ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላጢ ከሱዳናዊ አቻቸው ጋር ጥቅምት 12 ባደረጉት የስልክ ውይይት የሁለቱ አገሮች ዓለም አቀፍ ድንበር እንዲከበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የግብፅ መከላከያ ሚኒስቴር በባህላዊ ቆፋሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ቢገልጽም የዚህን ጥቃት ኃላፊነት አልወሰደም።
