በፌስቡክ ልመና ያቀረበች እናት ከማታውቀው ሰው ኩላሊት ተለግሳ ዳነች
የ41 ዓመቷ ካረን ዴቪ፡ ጋሪ ሳመርፊልድ የተባለ ሰው አንዱን ኩላሊቱን ለግሷታል

በኩላሊት ሕመም ምክንያት በፌስቡክ የተስፋ መቁረጥ ልመና ያቀረበች የአራት ልጆች እናት፡ ፈጽሞ የማታውቀው ሰው ኩላሊቱን ሊሰጣት ፈቃደኛ ከሆነ በኋላ፡ ሕይወቷን ያተረፈ የንቅለ ተከላ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል።
የ41 ዓመቷ ካረን ዴቪ በፌስቡክ ባሰፈረችው ጽሑፍ፡ ቤተሰቤን ያለ እናት መተው አልፈልግም ብላ ነበር። ይህን ያየው ጋሪ ሳመርፊልድ የተባለ ሰው በሐምሌ ወር አንዱን ኩላሊቱን ለግሷታል።
ጋሪ ስለ ወሰደው እርምጃ ሲናገር፡ ይህች ሴት እኔ ሁለት ኩላሊት ከሚያስፈልገኝ በላይ አንዷ ለእሷ ይበልጥ ታስፈልጋታለች ብዬ አሰብኩ ብሏል። የካረን ቤተሰቦች ለልግስናው በምንም ሊክሱት እንደማይችሉ ገልጸዋል።
የብሪታንያ የደምና የአካል ንቅለ ተከላ ተቋም ሪፖርት እንደሚያሳየው፡ ከሞተ ሰው ኩላሊት ለማግኘት በአማካይ ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት ይወስዳል፤ በሕይወት ያለ ለጋሽ ሲገኝ ግን ሂደቱ ወደ ሦስት እስከ ስድስት ወራት ያጥራል። ካረን ከ10 ዓመት በፊት የልብ ንቅለ ተከላ ተደርጎላት ነበር።
