ግብጽ ሠራዊቷን ወደ ሶማሊያ ለማሰማራት እየተዘጋጀች መሆኑ ተገለጸ
አማካሪዎች፡ አሰልጣኞችና መኮንኖች ይገኙበታል፤ በሴልኬድ አካባቢ ሊሰፍሩ እንደሚችሉ ተነግሯል
በአካባቢው የጸጥታና የመከላከያ ሪፖርቶች መሠረት፡ ወታደራዊ አማካሪዎች፡ አሰልጣኞችና መኮንኖች ያካተቱ የቴክኒክ ቡድኖች ወደ ሶማሊያ ለመሰማራት ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው ተገልጿል።
ስምሪቱ፡ በሁለቱ አገራት መካከል እየጨመረ በሄደው የጸጥታና የመከላከያ ትብብር ውስጥ፡ እንዲሁም ግብጽ በአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በሶማሊያ በመሳተፏ የሚጠበቅ መሆኑን ሪፖርቶቹ ያመለክታሉ።
ግብጽ ምን ያህል ሠራዊት ለማሰማራት እንዳቀደች በይፋ ባትገልጽም፡ ኃይሎቹ በመካከለኛው ሸበሌ ግዛት በሰሜናዊ ሞቃዲሾ በሚገኘው የሴልኬድ አካባቢ ሊሰፍሩ እንደሚችሉ ተነግሯል።
የግብጽ ወታደራዊ ልዑክ መስከረም 20 ወደ ሞቃዲሾ ገብቶ ከሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አሕመድ ሞዓሊም ፊቂ ጋር መገናኘቱ የሚታወስ ሲሆን፡ ይህ ስምሪት ከተረጋገጠ በ2024 ከተፈረመው የሁለትዮሽ ወታደራዊ ስምምነት ወዲህ ትልቁ መስፋፋት ይሆናል።
