ቻይናና ሰሜን ኮሪያን የሚያገናኝ ዘመናዊ ድልድይ ተከፈተ
ተግባራዊነቱ ዘግይቶ የቆየው ድልድይ የሁለቱን አገሮች ኢኮኖሚና የሕዝቦቻቸውን ግንኙነት ያሰፋል ተብሏል።

የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ አካል፡ የሚያገናኛቸውን ዘመናዊ ድልድይ ከፈቱ።
ተግባራዊነቱ ዘግይቶ የቆየው ይህ ድልድይ፡ የሁለቱን አገሮች ኢኮኖሚ ከማሳደግ ባሻገር የሕዝቦቻቸውን ግንኙነት እንደሚያሰፋ ተገልጿል።
በየብስና በባሕር የሚዋሰኑት ቻይናና ሰሜን ኮሪያ መደበኛ የአየርና የባቡር እንቅስቃሴ እንዳላቸው ይታወቃል።
