አሜሪካ ለጄኔራል አልቡርሃን የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ቪዛ ከለከለች
ዋሽንግተን፡ ሁለቱም ጄኔራሎች ሱዳንን የመምራት ሕጋዊም ሆነ ሞራላዊ ብቃት የላቸውም ስትል ገለጸች።

የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ ሁለቱም የሱዳን ጦር መሪዎች ጄኔራል አልቡርሃንና የተፋጠነ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች አዛዥ ሔመድቲ የሱዳን ሕጋዊ ሀገራዊ መሪዎች አለመሆናቸውን በይፋ አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶማስ ፒጎት በሰጡት መግለጫ፣ በጦርነት ላይ የሚገኙት ኃይሎች ቅድመ ሁኔታ የሌለው ሰብአዊ የተኩስ አቁም ለመስማማት ይልቅ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።
የትራምፕ አስተዳደር የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሣሪያ እገዳ ወደ መላው ሱዳን እንዲስፋፋ ጥሪ እያደረገ መሆኑንና፣ ጦርነቱን በሚደግፉ አካላት ላይ ከባድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
የዋሽንግተን የመጨረሻ ዓላማ፣ ሥልጣን ለሱዳን ሕዝብ ተላልፎ የሲቪል የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
