ሁለት አሜሪካውያን የ2026 የኢኮኖሚ ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ሮበርት ሆልና ማይክል ዉድፎርድ 1.2 ሚሊዮን ዶላር በጋራ ተሸልመዋል።

ሁለት አሜሪካውያን ምሁራን የ2026 የኢኮኖሚ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።
ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲን ለማሻሻል የሚረዳ የተሻለ አሠራር በማስተዋወቃቸው በየዓመቱ በስዊድን ለሚሰጠው ዓለም አቀፍ ሽልማት መብቃታቸው ተገልጿል።
አሸናፊዎቹ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲው ሮበርት ኢ. ሆልና የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲው ማይክል ዉድፎርድ ናቸው።
በዚህም ሁለቱ በጋራ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ተሸልመዋል።
የ2025 የኢኮኖሚ ኖቤል ሽልማትን ፈረንሳዊ፡ ሆላንዳዊና ካናዳዊ ምሁራን በጋራ ማሸነፋቸው ይታወሳል።
