ሳዑዲ ዓረቢያ፡ ቱርክና ፓኪስታን አስቸኳይ ወታደራዊ ስብሰባ ያደርጋሉ
ስብሰባው፡ በሦስቱ ሀገራት የተፈረመው የጋራ የመካ መከላከያ ስምምነት አካል መሆኑ ተገልጿል።

በቅርቡ በየመን በሚገኙ የሑቲ ታጣቂዎች በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ፡ የሳዑዲ ዓረቢያ፡ የቱርክና የፓኪስታን ወታደራዊ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹማምንት አስቸኳይ ወታደራዊ ስብሰባ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህ አስቸኳይ ወታደራዊ ስብሰባ፡ በሦስቱ ሀገራት የተፈረመው የጋራ የመካ መከላከያ ስምምነት አካል መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ስምምነት፡ በአዲሱ ቃል ኪዳን አባል በሆነች በማንኛዋም ሀገር ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሁሉም አባላት ላይ እንደተፈጸመ ጥቃት ይቆጠራል የሚል አንቀጽ ያካተተ በመሆኑ፡ የሑቲ ጥቃት ከሦስቱ ሀገራት የጋራ ወታደራዊ ምላሽ እንዲሰጥ ሊገፋፋ እንደሚችል ይገለጻል።
ሐሙስ መስከረም 24 በኒው ዮርክ በሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ቋሚ መልእክተኛ ጽሕፈት ቤት፡ የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሳል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድ፡ የፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ኢስሐቅ ዳር እና የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ከፍተኛ ደረጃ ያለው የሦስትዮሽ ስብሰባ አካሂደዋል።
ሚኒስትሮቹ፡ የመካን ከተማና በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ሲቪልና ኢኮኖሚያዊ ተቋማትን ዓላማ ያደረገውን ጥቃት በጥብቅ አውግዘው፡ ሀገሪቱ በተባበሩት መንግሥታት ቻርተር አንቀጽ 51 መሠረት ሉዓላዊነቷንና ደኅንነቷን ለመከላከል ሙሉ መብት እንዳላት አረጋግጠዋል።

