በሪያድ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሳይል ጥቃት፡ 12 ሰዎች ተገደሉ
ወደ 310 የሚጠጉ ቆስለዋል፤ አውሮፕላን ማረፊያው ሥራውን ለጊዜው አቋርጧል

በሪያድ ከተማ በሚገኘው የንጉሥ ካልድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተፈጸመ የሚሳይል ጥቃት ከባድ የሰውና የንብረት ጉዳት ደርሷል።
በጥቅምት 11ኙ ጥቃት፡ እስካሁን 12 ሰዎች መገደላቸውንና ወደ 310 የሚጠጉ መቁሰላቸውን የዜና ማሰራጫዎች የሳዑዲ የአቪዬሽን ባለሥልጣናትን ጠቅሰው አስታውቀዋል።
ከሟቾቹ አራቱ የሳዑዲ ዜጎች ሲሆኑ፡ የቀሩት ስምንት የሌሎች አገራት ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል። አውሮፕላን ማረፊያው ሥራውን ለጊዜው አቁሟል።
የሳዑዲ መንግሥት ጥቃቱን የፈጸመው የሑቲ ታጣቂ ቡድን መሆኑን ከሷል። ተመድ ጥቃቱን አጥብቆ ሲያወግዝ፡ አሜሪካ በሑቲ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ጠቁማለች።
