ግብፅ ለኢትዮጵያ፡ ግድብና መንገድ አንድ አይደሉም
ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላም፣ ከአሥር በላይ አገራት የሚጋሩት ወንዝ የአንዲት አገር ሉዓላዊ መብት አይደለም ብለዋል።

የግብፅ የውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላም፣ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች በአገራቸው ውስጥ መንገድ መዘርጋትና በአንድ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ላይ ግድብ መገንባት ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን መረዳት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የእኔ ትርጓሜ አይደለም፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ከአሥር በላይ አገራት በሚጋሩት ወንዝ ላይ ግድብ መገንባት የአንዲት አገር ሉዓላዊ መብት ነው የሚለው ሐሳብ ከየት እንደመጣ አላውቅም ሲሉ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በሚል ዓላማ መገንባቷን ጠቅሰው፣ ነገር ግን እየተመነጨ ያለው ኃይል በቢትኮይን ማዕድን ቁፋሮ ላይ እየዋለ መሆኑን ጠቁመዋል።
ግብፅ በደቡብ ሱዳን ለመገንባት የታሰበውን ግድብ እንደማትቃወም በይፋ አሳውቀዋል።
