ሚኒስትር የማነ፡ የኢትዮጵያ ጄኔራሎች ፉከራ የወረራ አዋጅ ነው አሉ
የአየር ኃይል አዛዥ ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፡ የባሕር በራችንን ለመክፈት በዋዜማ ላይ ነን ብለዋል

ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የባሕር በራችንንና ሉዓላዊነታችንን ለመመለስ በዋዜማ ላይ ነን ካሉ በኋላ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር የማነ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት አጭር ጽሑፍ፡ አዛዡ የአንድ የተመድ አባል አገር የግዛት አንድነትን የሚመለከተውን ዓለም አቀፍ ሕግና የተመድ ቻርተርን የሚጥስ የዓሰብ ወረራ ለማወጅ በድፍረት የቀረበ መሪ መሆኑን ገልጸዋል።
ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮንኖች ተደጋጋሚ መግለጫዎች የሚሰጡት፡ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ እያዘጋጀ ነው ለሚባለው የጦርነት ዝግጅት ተዓማኒነት ለመስጠት መሆኑንም አብራርተዋል።
ከዚህ ቀደም ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፡ የመጨረሻ መድረሻችን ዓሰብ ናት፤ መቀሌ መሸጋገሪያ ብቻ ናት ሲሉ መፎከራቸው ይታወሳል።
