ጦርነትና ግጭቶች በአካባቢ ላይ አሳሳቢ ጉዳት እያደረሱ መሆኑ ተገለጸ
የዩክሬን ጦርነት ከ310 ሚሊዮን ቶን በላይ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አየር ለቋል።

ጦርነትና ግጭቶች ከሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራቸው በተጨማሪ፡ በአካባቢ ላይ አሳሳቢ ውድመት እያደረሱ መሆኑን ሪፖርቶች ገልጸዋል።
በሪፖርቶቹ መሠረት፡ በ2025 እና በ2026 ከ5 በመቶ በላይ የሚሆነው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የብክለት ጋዝ ልቀት በጦርነትና በግጭት የተከሰተ መሆኑ ታውቋል።
ከ2022 ጀምሮ የቀጠለው የዩክሬን ጦርነት ከ310 ሚሊዮን ቶን በላይ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አየር መልቀቁንና፡ ጦርነቱ ባስከተለው ቃጠሎ ከ100 ሺህ ሄክታር በላይ ደን መውደሙ ይገለጻል።
በመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ደግሞ፡ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ 400 ሚሊዮን ኩንታል ያህል የብክለት ጋዝ ወደ አየር መቀላቀሉን የአካባቢ ባለሙያዎች ይጠቅሳሉ።
ፈንጂዎች በውሃና በመሬት ላይ የሚያስከትሉት አደገኛ ብክለት፡ በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱንም ባለሙያዎቹ ይገልጻሉ።
