አሜሪካ ከመካከለኛው እስያ ሀገራት ጋር ስምምነቶችን ተፈራረመች
ማርኮ ሩቢዮ በኢንቨስትመንት፡ በብርቅዬ ማዕድናትና በመሠረተ ልማት ላይ ያተኮሩ ስምምነቶችን ፈርመዋል።

አሜሪካ ከመካከለኛው እስያ ቀጣና ሀገራት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሳደግ እንደምትሠራ አስታውቃለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጥቅምት 19 ከኡዝቤኪስታን፡ ካዛኪስታን፡ ታጂኪስታን፡ ቱርክሜኒስታንና ኪርጊስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በኡዝቤኪስታን በተካሄደው ስብሰባ፡ ኢንቨስትመንትን፡ ብርቅዬ ማዕድናትንና መሠረተ ልማትን ጨምሮ በበርካታ ስምምነቶች ላይ መፈረሙ ተገልጿል።
የስምምነቱ አካል በመሆን፡ አሜሪካ የሀገራቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች።
አሜሪካ በ2025 ከአምስቱ ሀገራት ጋር 10 ቢሊዮን ዶላር ያህል፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ደግሞ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የንግድ ልውውጥ ማድረጓን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።

