አሜሪካ በዩክሬን ጦርነት የራሷን መንገድ እየተከተለች መሆኑ ተገለጸ
የታገደውን የሩሲያ ካፒታል እንዲለቀቅ ያቀረበችውን ሐሳብ አውሮፓ አልተቀበለችውም።

የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት መሪዎች በብራስልስ ተሰብስበው ከዩክሬን ጎን መሆናቸውን በወሰኑበት ወቅት፡ አሜሪካ የራሷን መንገድ እየተከተለች መሆኑን ዘ ፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ዘግቧል።
አሜሪካ የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም ግፊት ለመፍጠር፡ በአውሮፓ ኅብረት የታገደው በቢሊዮን የሚቆጠር የሩሲያ ካፒታል እንዲለቀቅ ሐሳብ አቅርባለች።
ሩሲያ፡ የታገደው ገንዘብ ለዩክሬን ከተሰጠ ከባድ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቃለች።
የዩክሬን አጋር የሆኑት የአውሮፓ ሀገራት ግን ሐሳቡን አልተቀበሉትም። የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሬድሪክ መርዝ፡ የታገደው ካፒታል የአውሮፓ ኅብረትን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ገልጸዋል።
የምዕራብ ሀገራት የዩክሬን ጦርነት በ2022 ከተቀሰቀሰ በኋላ 300 ቢሊዮን ዶላር ያህል የሚገመት የሩሲያ ካፒታል ማገዳቸው ይታወሳል። ሞስኮ እርምጃውን ግልጽ ስርቆት ስትል አውግዛለች።
