አሜሪካውያን ትግራዋያን ለማርኮ ሩቢዮ ግልጽ ደብዳቤ ጻፉ
በትግራይ ሁለተኛ ዙር ጅምላ ጭፍጨፋ እንዳይፈጸም አሳስበዋል።

የአሜሪካውያን ትግራዋያን ማኅበረሰብ ተወካዮች፡ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስቸኳይ ግልጽ ደብዳቤ አቅርበዋል።
ደብዳቤው፡ ሩቢዮ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ጥቅምት 14 ያደረጉትን ይፋዊ ግንኙነት በተመለከተ ጥልቅ ስጋታቸውን ይገልጻል።
ትግራይ ተገንጣይም ሆነ አሸባሪ አለመሆኗን በመግለጽ፡ በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የድሮን ጥቃትና የፕሪቶሪያ ስምምነት ጥሰት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወታደራዊ እንቅስቃሴ ተሰማርቶ መሆኑንና ለዚህ በአሜሪካ የተሠሩ የቦይንግ አውሮፕላኖችን መጠቀሙ ሊጣራ እንደሚገባም ጠይቀዋል።
አቤቱታው በኢትዮጵያ ወይም በኤርትራ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑንና ለፍትሕ፡ ለተጠያቂነትና ለዘላቂ ሰላም ያለመ መሆኑን በመግለጽ፡ ከሩቢዮ ጋር ፊት ለፊት ለመገናኘት እየጠበቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
