ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጎን መሆኗን አረጋገጠች
ፕሬዚዳንት ኢሮ፡ ጎረቤት ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

የሶማሊላንድ ርዕሰ መስተዳድር ፕሬዚዳንት አብዲራሕማን መሐመድ አብዱላሂ፡ አስተዳደራቸው በሚያጋጥሙ የደህንነት ሁኔታዎች ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል።
ኢሮ በሚል ቅጽል ስም የሚጠሩት ፕሬዚዳንቱ በሃርጌሳ በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው ሆነው ባስተላለፉት መረጃ፡ የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለሶማሊላንድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ስም ያልጠቀሷቸው ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና እንዲቆም አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል። ይህን አስተያየት የሰጡት በዋሽንግተን ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሃርጌሳ ከተመለሱ በኋላ ነው።
በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል። የሶማሊላንድ የሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋር በወታደራዊ ትብብር ላይ ያተኮረ ግንኙነት ማድረጋቸው ተገልጿል።
ሶማሊላንድን እንደ ሀገር ተቀብላ ይፋዊ ኤምባሲ የከፈተች ብቸኛ ሀገር እስራኤል መሆኗ ይታወቃል።
