ሲሲ ለሳዑዲ ዓረቢያ ወታደራዊ ድጋፍ የሚፈቅድ ውሳኔ ከፓርላማ ጠየቁ
ሪያድ ድጋፍ ከጠየቀች የግብፅ ሠራዊት እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል አስቸኳይ ስብሰባ እንዲካሄድ ጠይቀዋል።

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ አልሲሲ፡ ለሳዑዲ ዓረቢያ ሊሰጥ ስለሚችል ወታደራዊ ድጋፍ ከሀገሪቱ ምክር ቤት ፈቃድ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
አልሲሲ ይህን የገለጹት፡ ዋናው የግብፅ ወታደራዊ አካዳሚ በ30 ወራት ውስጥ የወደፊት መሪዎችን ለማሰልጠን ያወጣውን እቅድ ባቀረቡበት ወቅት ነው።
ሪያድ የድጋፍ ጥያቄ ካቀረበች፡ የግብፅ ሠራዊት ለሳዑዲ ዓረቢያ ድጋፍ እንዲያደርግ ስልጣን የሚሰጥ አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ እንዲካሄድ ጠይቀዋል።
የግብፅ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፡ የሳዑዲ ዓረቢያን ደህንነት፡ መረጋጋትና የግዛት አንድነት ለመጠበቅ ሁሉንም አስፈላጊ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።
የሀገሪቱ ፓርላማ በዚህ ጉዳይ ጥቅምት 26 ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገልጿል። ይህ የመጣው በኢራን የሚደገፉ የየመን ሑቲ ታጣቂዎች በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ የሚያደርሱት ጥቃት እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው።

