የሩሲያና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቴህራን ተገናኙ
ባለፈው ዓመት የተደረሰውን ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተግባራዊነት ለማፋጠን ተወያይተዋል።

የሩሲያና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፡ ጥቅምት 19 በቴህራን ከተማ የምክክር ስብሰባ አካሂደዋል።
ውይይቱ ባለፈው ዓመት የተደረሰውን የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተግባራዊነት ማፋጠን እንደሚያካትት ተገልጿል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና ፕሬዚዳንት መስዑድ ፐዘሽክያን በጥር 2025 ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የሚቆይ ስትራቴጂያዊ ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል።
ሰርጌይ ላቭሮቭና አባስ አራቅጂ በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች፡ በተለይም በመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሀገራት የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ በውይይት ብቻ ሊፈታ እንደሚችል አስምረዋል። ሚኒስትሮቹ በዚህ ዓመት አራት ጊዜ በአካል እና 14 ጊዜ በስልክ መወያየታቸውን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።

