ጌታቸው ረዳ በራያ ተቃውሞ እንደገጠመው ተገለጸ
ለአባቱ ሐዘን ያደረገው ጉብኝት፤ የራያ ሕዝብ የፖለቲካ ጥሪውን አልተቀበለም ተብሏል

የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሊቀመንበርና አሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪ የሆነው ጌታቸው ረዳ፡ ወደ አላማጣ ባደረገው ጉብኝት ተቃውሞ ገጥሞታል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ለአባቱ ሐዘን መድረስ ቢመስልም፡ በተግባር ግን በአካባቢው አዲስ የፖለቲካ እንቅስቃሴና ተጽዕኖ ለመፍጠር ያለመ እንደነበር ዘገባዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሰው አስረድተዋል።
የአካባቢው ሕዝብ ለቀረበለት የፖለቲካ ጥሪ ጊዜ እንደሌለው በግልጽ መግለጹን ዘገባዎቹ አስታውቀዋል።
ተቃውሞው፡ የራያ ሕዝብ ከዚህ ቀደም የነበረውን የፖለቲካ ሂደትና የሥልጣን መዋቅር እንደማይቀበልና ለራሱ ውሳኔ እንደሚቆም የሚያሳይ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
