‘ትግራይ ሰፈራችን ናት’ — የፌደራል ሠራዊት አዛዦች
ትግራይን ለፌደራል መንግሥት ወሳኝ ወታደራዊ ሰፈር ለማድረግ ሰፊ እቅድ መውጣቱን ምንጮች ገለጹ።

ትግራይን ለፌደራል መንግሥት ወሳኝ ወታደራዊ ሰፈር ለማድረግ ሰፊ እቅዶች መውጣታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ባለሥልጣናት የተገኙ ምንጮችን ጠቅሰው ሪፖርቶች አስታወቁ።
ፌደራሉ በመቀሌ ልዩ የሆነ ወታደራዊ ሰፈር ለማቋቋም ዝግጅት መጀመሩን የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በመያዝ ወደ ‘የሰላም ኃይሎች’ ወደተባለው ቡድን እንዲቀላቀሉ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ብልጽግና ትግራይ በኮማንድ ፖስት ሥር እንድትቆይ መመሪያ ሰጥቷል። Tigray Media Service እንደዘገበው ዶ/ር አብርሃም በላይና አቶ አታክልቲ ኃይለሥላሴ ኮማንድ ፖስቱን እንዲመሩ ተሾመዋል።
ናትና ቲቪ ዘገባውን በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም።
