የኢትዮጵያ ጦር አዛዦች መግለጫ የኤርትራን ሉዓላዊነት በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ ጥሎታል
የአየር ኃይል አዛዥ ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፡ ኢትዮጵያ የባሕር በሯን የምትከፍትበት ቀን ቀርቧል ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር አንቀጽ 2(4)ንና የአፍሪካ ኅብረት ስምምነቶችን በመጣስ፡ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አመራሮች ስለ አሰብ ወደብ በተከታታይ የሚሰጡት የጦርነት መግለጫ በቀጣናው ያለውን የጸጥታ ቀውስ የበለጠ እንዳባባሰው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ጄኔራል ይልማ መርዳሳ "ኢትዮጵያ ለረዥም ዓመታት ተዘግቶ የቆየውን የባሕር በሯን የምትከፍትበትና ሉዓላዊነቷን የምታረጋግጥበት ቀን ቀርቧል" ሲሉ ተናግረዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላም ለኢትዮጵያ ሠራዊት በሰጡት መመሪያ "ወደብ የከለከለንን አገር ልንወጋ እንችላለን" ማለታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ2023 ጀምሮ በፓርላማና በሕዝባዊ መድረኮች የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ ታሪካዊ መብት መሆኑንና በኃይልም ቢሆን የባሕር ድንበርና የባሕር ኃይል ሊኖራት እንደሚገባ ሲገልጹ ቆይተዋል።
ኤርትራ በዚህ ተከታታይ የጦርነት ዛቻ ራስን የመከላከልና ተመጣጣኝ የጸጥታ ጥንቃቄዎችን የመውሰድ ሙሉ ሕጋዊ መብት እንዳላት ሪፖርቱ ያስረዳል።
