የኤርትራ ሴቶች ማኅበር የብሪታንያ ቅርንጫፍ ዓመታዊ ግምገማውን በለንደን አካሄደ
130 የንዑስ ቅርንጫፍ ተወካዮች ተሳትፈዋል፤ የመንደፈራ ማሠልጠኛ ማዕከል ፕሮጀክት መሳካቱ ተነግሯል

የኤርትራ ሴቶች ማኅበር የታላቋ ብሪታንያ ቅርንጫፍ የዓመታዊ ተግባራቱን ግምገማ በለንደን ከተማ አካሂዷል። በስብሰባው 130 የንዑስ ቅርንጫፍ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በታላቋ ብሪታንያና አየርላንድ የኤርትራ ኤምባሲ ሥራ አስኪያጅ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፡ ንቃትና ድርጅት ጠንካራው ትጥቅ በመሆኑ በዚህ መስክ በተሻለ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የሕዝብና የማኅበረሰብ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ተወልደ ዮውሃንስ፡ ስለ አገሪቱና ቀጣናው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ፡ ተሳታፊዎች ጥልቅ ግምገማ አድርገው የሚቀጥለውን ዓመት ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።
የቅርንጫፉ ሊቀመንበር ባቀረበችው ሪፖርት፡ በ2026 የአባላትን ብቃትና ንቃት በማሳደግ፡ ድርጅቶችን በማስፋት፡ ወጣቶችን በማፍራት፡ በሕዝባዊ ዲፕሎማሲና የመንደፈራ ማሠልጠኛ ማዕከል ፕሮጀክትን በማሳካት የሚመሰገን ሥራ መከናወኑን ገልጻለች።
