ኤርትራ ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠንካራ ምላሽ ሰጠች
ሐዳስ ኤርትራ ጋዜጣ፡ ብልጽግና በኤርትራ ሕዝብ ላይ ያወጀውን ጦርነት ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በጻፈው ደብዳቤ ይፋ አድርጎታል ብሏል።

ኤርትራ በሐዳስ ኤርትራ ጋዜጣ በኩል ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠንካራ ምላሽ ሰጠች።
መግለጫው፡ ብልጽግና ከሦስት ዓመት በፊት በኤርትራ ሕዝብ ላይ ያወጀውን ጦርነት በቅርቡ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ በመላክ ይፋ እንዳደረገው ይገልጻል።
ቡድኑ በደብዳቤው የኤርትራን ሕዝብ ለመውረር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ቃላት አሳውቋል ይላል መግለጫው። በዚህ ውሳኔውም በኢትዮጵያ ሕዝቦች (ትግራይ፡ አማራ፡ አፋር፡ ኦሮሞ) እንዲሁም በሱዳን ሕዝብ ላይ ያወጀውን ጦርነት ወደ ኤርትራ ለማስፋፋት መወሰኑን በይፋ ነግሯል።
መግለጫው አክሎ፡ የኤርትራ ሕዝብ ረዥም ጦርነት ያለፈና መዘዙን በሚገባ የሚያውቅ በመሆኑ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከፍተኛ ራስን የመግዛት ትዕግሥት ሲያሳይ መቆየቱን ያስረዳል።
