የኤርትራ መንግሥት በሐተታ ኢትዮጵያን ወቀሰ
ብልጽግና በዘመናዊ ትጥቅና በሠራዊት ሥልጠና ላይ ከአቅሙ በላይ ወጪ እያደረገ ነው ተብሏል።

የኤርትራ መንግሥት ባወጣው ሐተታ፡ ብልጽግና ከ2020 እስከ 2022 በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት ካበቃ በኋላ ባለፉት ሦስት ዓመታት ራሱ ባስነሳው ወታደራዊ ጀብዱ ተጠምዶ መቆየቱን ገልጿል።
ሐተታው እንደጠቀሰው፡ በ2026 በመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ብቻ የ365 አውሮፕላኖች ጭነት ወታደራዊ ቁሳቁስ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ተቀብሏል። ይህ ወጪ ከኢትዮጵያ አቅም በላይ በመሆኑ፡ ቀጣናውንና ሀብቱን ለመቆጣጠር በሚፈልጉ ኃይሎች የሚደረግ መሆኑን ያስረዳል።
አክሎም፡ ሥርዓቱ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከበርካታ ለጋሾች በድምሩ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን ይጠቅሳል። በተመሳሳይ ጊዜ ግን 21.4 ሚሊዮን ገደማ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሳሳቢ ደረጃ ወድቆ ሕልውናው በሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ የተመሠረተ ሆኗል።
