ግብፅና ሶማሊያ ስለ ቀይ ባሕር ደህንነት ተወያዩ
የኤል አላሜይን ጉባኤ ውጤቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

ግብፅና ሶማሊያ የኤል አላሜይን ጉባኤ ውጤቶችን በመተግበርና በቀይ ባሕር ደህንነት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደልዓጢ ከሶማሊያ አቻቸው አብዲሰላም አሊ ጋር እሁድ በስልክ ባደረጉት ንግግር፡ በቀንደ አፍሪካና በቀይ ባሕር ያሉ ስትራቴጂያዊ እድገቶችን በጥልቀት ተወያይተዋል።
ፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ አልሲሲ በጥቅምት መጀመሪያ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፡ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድና ከሱዳን የሽግግር ምክር ቤት ኃላፊ አብዱልፈታሕ አልቡርሃን ጋር የጋራ ጉባኤ ማስተናገዳቸው ይታወሳል።
ሚኒስትር አብደልዓጢ፡ ግብፅ ለሶማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ያላት ድጋፍ ቀጣይ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አዲሱ ስትራቴጂያዊ ቃልኪዳን፡ የቀይ ባሕር አስተዳደር በባሕር ዳርቻ ያሉ ሀገራት ብቻ ኃላፊነት መሆኑን ያጸናል።
